ኪዳነምሕረት እናቴ አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ የፍቅር /የሰላም/ እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ /2/ የተገለጠዉ ብርሃን በምሥራቅ የተወለደዉ በፍቅር ሰንሰለት አስሮ ዓለምን ሁሉ አዳነዉ /2/ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ በረሃዉን ባሰብኩት ጊዜ የግብፅን የአሸዋ ግለት አንቺ ትንሽ ብላቴና %ረ እንዴት ቻልሽዉ በእዉነት /2/ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ዝም ብዬ ይደንቀኛል የአምላክን ሥራ ሳስበዉ ምክንያት አንቺን አድርጎ ይህንን ዓለም አዳነዉ/2/