ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ ምግብና መጠጤ አምላኬ ነዉና ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና /፪/ ሕዝቡ ተሰብስቦ በቤተክርስቲያን ስ!ዘምር ደስ ይላል በአንድነት ሆነን በረከት ይሞላል ዝማሬዉ ይገርማል ከእጣኑ ጋራ ወደላይ ይወጣል ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ ምግብና መጠጤ አምላኬ ነዉና ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና /፪/ ቀሳዉስቱ ሌሊት ማኀሌት ሲያቀርቡ ከመላእክቱ ጋር ወረብ ሲወርቡ ብርሃኑን ለብሰን በደስታ ስንዘምር ትዝታዉ ልዮ ነዉ ሕሊና ሲሰዉር /2/ ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ ምግብና መጠጤ አምላኬ ነዉና ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና /፪/ ራእይ ነዉና ኑና ተመልከቱ ሰዎች ሲዘምሩ እንደመላእክቱ የጽጌዉ ማኅሌት የትንሣኤዉ ደስታ /2/ ልዮ ዝማሬ ነዉ እንዳይመስለን ተርታ /2/