ከጣራን ዉጡ ከነዓን ግቡ ወደ ጽድቅ ሕይወት ዛሬ ቅረቡ ካራን ጣዖት ነዉ የሚመለከዉ የአሕዛብ ሀገር የሙት መንደር ነዉ /2/ እንደአባታችን እንደ አብርሃም ወገኖች ዉጡ ከካራን ዓለም የግፍ እንጅራ ይብቃችሁና ከካራን ዉጡ በአምላክ ጐዳና አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የጣዖት ምስል ከሚሸጥበት ዓለም በዝሙት ከሚነድበት ከሰዶም መንደር ከካራ ዉጡ የኃጢአትን ሰንሰል ዛሬ ቁረጡ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የኃጢአት ዓለም ዛሬ ይብቃና የፍቅር ሕይወት እንልበስና ከካራን መንደር በፍጥነት ወጥተን ከነዓን ገብተን ማደር አለብን አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ማርና ወተት ከሚፈልቅበት ሰዎች በፍቅር ከሚኖሩበት ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም ዛሬ ብንገባ እናገኛለን የአምላክን ሰላም