ለንስሓ ሞት ቷብቃኝ /2/ በሂሶኘ እርጨኝ እጠበኝ እንደ በረዶ አንሳኝ /2/ አመፃዬ በዛ ኃጢአትን ጨመርኩኝ ልቤ ደነደነ ክፋትን ፈጸምኩኝ እንደ ፈርዖን ልቤ እንዳይጸናብኝ አድነኝ እንደ ኖኅ አምላክ ራራልኝ አድነኝ /3/ ስለ ድንግል ብለህ አድነኝ አድነኝ /2/ ስለ ሳድቃን ብለህ አድነኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ኃጢአቴም በረታ ሰለጠነብኝ ከቃልህ አስወጣኝ ሕግህን ጣስኩኝ እንደነነዌ& ሕዝብ ንስሓን ስጠኝ ምሕረትህን ልከህ ልቤን ስበርልኝ አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ አድነኝ /2/ እንደ ምሕረትህ አድነኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ያደፈዉ ገላዬን አንተ አጥራልኝ ከሰዶም ገሞራ እንዳይብስብኝ መንገድና ሕይወት አንተ ነህ ምራኝ የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሓ ስጠኝ አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ አድነኝ /3/ ስለ እናትህ ብለህ አድነኝ አድነኝ /2/ ስለ ሳድቃን ብለህ አድነኝ