አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል /2/ ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነህ ይለኛል ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነሽ ይለኛል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ በበደል ጉራንጉር በኃጢአት ጫካ ብጠፋበት እንኳን አልተወኝም ለካ ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል ለ ስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ለሥልጣን ለክብር ብዬ ስክደዉ ለገንዘብ አድልቼ እኔ ስረሳዉ ለእኔ ያለዉ ፍቅር አልቀነሰብኝም ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለዉ ወሰን ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን በሕይወቴ ሁሉ ፍጹም ለመራኝ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁኝ