አምላካችን ተመስገን /2/ ለዛሬ ያደረስከን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዚህ ቀን ያደረስከን በኃጢአት ስንማቅቅ በምሕረትህ ጠራኸን በዓለም ስንባዝን ነበር በይቅርታህ መራኸን አምላክ ሆይ ተመስገን ትዕግሥትህ ብዙ ነው አያልቅም ርኅራኄህ የምንከፍልህ ምን ይሆን ብዙ ነዉ ውለታህ አምላክ ሆይ ተመስገን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዛሬ ያደረስከን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዚህ ቀን ያደረስከን ከቶ የማትፈልግ ከሰው ልጆች ወረታ ቸር ፈጣሪ ነህና ሥራህ ድንቅ ነዉ ጌታ አምላክ ሆይ ተመስገን ይቅር ባይ አምላካችን ሆይ አንተን እናመልካለን ከመዓትህ ታግሰህ ሁሉንም ይቅር አልከን አምላክ ሆይ ተመስገን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዛሬ ያደረስከን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዚህ ቀን ያደረስከን ኃጢአታችን ጨለማ ቢያደርገዉ ኑሮአችንን በአንተ ተጎናጽፈናል የማዳንን ብርሃን አምላክ ሆይ ተመስገን ስለአደረክልን ሁሉ ስለ ግሩም ሥራህ የራስህን እንስጥህ ተመስገን እንበልህ አምላካችን ተመስገን /2/ ለዛሬ ያደረስከን አምላካችን ተመስገን /2/ ለዚህ ቀን ያደረስከን