colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ባርከን

ባርከን ባርከን ልጆችህን ባርከን /2/ በቅዱስ መንፈስህ አንድ ሐሳብ አድርገን /4/ ባርኪን ባርኪን ልጆችሽን ባርኪን /2/ ድንግል ሆይ በምልጃሽ አንድ ሐሳብ አድርጊን ድንግል ሆይ በምልጃሽ ከልጅሽ አስታርቂን ጥሪህን ስንሰማ ወደቷንተ እንድንመጣ በሕግህ ልንኖር ከቤትህ ሳንወጣ በሕይወት ስንደክም እንዳንጠፋ በዓለም እርዳን ፈጣሪያችን ቸሩ መድኃኔዓለም ከተፈረደብን የባርነት ሕይወት ከመጣብን መርገም በመብል ምክንያት ከሲኦል እስራት እኛ የዳንብሽ ድንግል ሆይ ሁል ጊዜ አይለየን ምልጃሽ። አንድነት ስናጣ ፍቅር ስትመነምን በምግባር ስንደክም ሲጐድል እምነታችን በሥጋችን ፈቃድ ወድቀን እንዳንጠፋ በምሕረትህ ጐብኘን አንተ ሁነን ተስፋ ርኅርኅተ ኅሊና ቅድስት እናታችን አሳስቢ ሁል ጊዜ ስለ ኃጢአታችን ሊያድነን ነዉና ክርስቶስ መሞቱ አሳስቢ እመአምላክ ድንግል ወላዲቱ