አብርሃምን ከካራን የጠራኸዉ ጌታ ለሙሴ በሲና የሆንከዉ መከታ ልጠፋ ነዉና በሥጋ ፍላጎት የይስሐቅም ጌታ ሕይወቴን ታደጋት /2/ የኤርትራን ባሕር በኃይልህ የከፈልክ በሲና በረሃ ሕዝብህን የመገብክ ኖኅ ከጥፋት ዉኃ የዳነብህ አምላክ ሎጥን እንዳዳንከዉ ፍጹም ምሕረትን ላክ /2/ የተነበዮልህ ነቢያት በሙሉ አምላክ ሰዉ ይሆናል ይወለዳል ሲሉ ከዓሣ አንበሪ ሆድ ዮናስን ያወጣህ ዓለም ልትዉጠኝ ነው አይለየኝ ጸጋህ /2/ ሥጋን ተዋሕደህ በወሰንከዉ ሰዓት የሞትክልኝ አምላክ ያዳንከኝ ከሞት ሞት እንደወንጌልህ ሕግ የምኖር አድርገኝ በመጨረሻዉ ቀን በቀኝህ አድርገኝ /2/ አልቻልኩኝምና ልፈጽም ሕግህን የሐዋርያት አጽናኝ ስጠኝ ብርታትህን ምግባረ ጎደሎ ሆኛለሁኝና የቅዱሳን አምላክ እርዳኝ እንድጸና /2/