ወላዲተ አምላክ የሁሉ እመቤት ለምኝልን ለእኛ ከልጅሽ ምሕረት በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት እንዲያወጣን ነጻ ከፍርድ ቅጣት ድንግል ሆይ ለምኝልን /2/ በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን በምድራዊ ምኞት ናዉዞ ልቦናችን ፍቅርና ትሕትና ጠፍቶ ከፊታችን ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ሥራችን አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የምስኪኖች ተስፋ የደካሞች ኃይል ጠዉልገናልና ጥላ ሁኚን ድንግል እምነት ጨምሪልን ልቦናችን ይጽና እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና አዝ ፥፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘለዓለም ተድላ በፍቅርሽ መልሺን ከሲኦል ጎዳና ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና