ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልኝም ዜና እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና /2/ ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ ፍጹም ትኅትናን ይዛ ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ ፍጹም በልቧ ሳትመኝ እንደ ቃልህ ይን አለችው በቃሉ ተማርኝ /2/ አዝ . . . ዓለም መድኃኒት ነውና ከአንቺ የሚወለደው መንፈስ ቅዱስ ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/ አዝ . . . እጹብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት እድል የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ ከሴቶች መኝከል /2/ አዝ . . . ጸጋን የተመላሽ ሆይ ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም ከአንቺ ጋር ነውና /፪/