ሰላም ላንቺ ይሁን (3) ማርያም ድንግል (2) የሴቶች መመኪያ የሴቶች አክሊል (2) ሰላም ላንቺ ይሁን (3) የሁሉ እመቤት /2/ የኃጥአን ተስፋ የጻድቃን(2) ሕይወት /2/ ሰላም ላንቺ ይሁን/3/ የሁሉ ወዳጅ/2/ የጽድቅ መሰላል የዓለም /2/ አማላጅ/2/ ሰላም ለወለድሽው/3/ አምላካችንን /2/ ሰማይና ምድር የማይችሉትን/2/ ሰላም እመቤት /3/ አምላክን የወለድሽ/2/ የሰማይ መላእክት የሚያመሰግኑሽ /2/ ሰላም ለመቤቴ /3/ አምላክ የመረጠሸ/2/ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ /2/ ነሽ/2/