እመቤታችን ላንቺ ስላምታ ይገባሻል/2/ ከሴቶች ሁሉ /3/ ተመርጠሻል ሐርና ወርቁን እያስማማች ስትፈትል /2/ ተዘጋጀላት/3/ የመመረጥ እድል እመቤታችን ------------ እያረጓጓት የሰማይ መላእክት /2/ ቤተ መቅደስ ኖረች/3/ አሥራ ሁለት ዓመት እመቤታችን ላንቺ------- መንፈስ ቅዱስ እንደቀረባት አውቆ ሰገደላት /3/ ዘካርያስ ታጥቆ እመቤታችን ላንቺ ------------- መንፈስ ቅዱስ እንደቀረባት አውቃ ተሳለመቻት /3/ ኤልሣቤጥም ታጥቃ እመቤታችን ላንቺ --------------- አያስደንቅም ወይ የማርያም ትኅትና ውኃ ስትቀዳ/3/ የአምላክ እናት ሁና እመቤታችን ላንቺ ----------- የምንጭ ውኃ ምሥጢር የሚያመለክተው/2/ የአምላክ መገኛ ምንጭ /3/ እርሷ መሆንዋን ነው እመቤታችን ላንቺ --------