ማርያም እመቤቴ የአምላክ እናት ማደሪያ የሆነኸው ዙፋን ለመለኮት ከሴቶች ሁሉ አንቺ ነሽ የተባረክሽ የነጻሽ በእውነት ከቶ እንደምን ቻልሽው መድኃኔዓለምን ሰማይና ምድር የማይችሉትን ለዚህ የተመረጥሽ ታላቋ እድለኛ ምሕረትን ከልጅሽ ለምኝልን ለኛ ማርያም እመቤቴ -------------- ምንኛ ድንቅ ነው ምሕረቱ የወልድ፣ ያንቺን ሥጋ ለብሶ ሲሆነን ዘመድ፡፡ ከዙፋኑ ወርዶ ያገለገለሽ የሕይወት ሙሽራ ማርያም አንቺ ነሽ ማርያም እመቤቴ -------------- የነቢያት ሞገስ የሐዋርያት የሰማእታት አክሊል የጻድቀን እናት የእኛ መመኪያችን የኃጥአን ተስፋ ወልድን በመውለድሽ ኃዘናችን ጠፋ ማርያም እመቤቴ ቅዱሳን በገነት ሲያመሰግኑሽ መላእክት በሰማይ ሲያገለግሉሽ እኛም የአዳም ልጆች ከመሬት ሆነን ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን ማርያም እመቤቴ --------