የዓለም መድኃኒት የተወለደብሽ አንቺ ቤተልሔም የተቀደስሽ ነሽ የአማልክት አምላክ ንጉሠ ነገሥት ኃያላን በሙሉ የሚሰግዱለት በጨርቅ ተጠቅልሎ ተኛ በበረት የዓለም መድኃኒት ----------------- አዋቂዎች ሁሉ በቅን አሳባቸው ወደአንቺ ተጓዙ ኮከብ ሲመራቸው/2/ የዓለም መድኃኒት --------------- ለተከታይ ትውልድ ምሣሌ ለመሆን ሰግደው ገበሩለት ወርቅ እጣን ከርቤን /2/ የዓለም መድኃኒት ------------------ የሚያድለው ጌታ እውቀት ለሕፃናት የሚመሰገን ነው በአፈ መላእክት ከእንስሳት ጋራ አደረ በበረት የዓለም መድኃኒት ---------------- ሥጋ ለብሶ ቢታይ ረቂቅ መለኮት በአንድ ላይ ዘመሩ ሰውና መላእክት /2/ የዓለም መድኃኒት------------------