ክርስቶስ በስምህ ይዘናል ቀኖና ስቅለት ትንሣኤህን እናያለንና ጾም ማለት እንግዲህ ይኸው ነው ሥርዓቱ ሐዋርያት ጾመው ለእኛ አበረከቱ ነፍስና ሥጋችን በመብል ተጣልተው ሽማግሌ ሆኖ ጾም አስታረቃቸው አብርው እያደሩ አብረው እይዋሉ አያምርም አይመስልም በመብል ሲጣሉ ነፍስም ከስጋዋ መለየቷን አውቃ የዓለም ተድላዋን ደስታዋን ንቃ በጾም በሱባኤ ትኖራለች ታጥቃ፡፡ ነፍስም ለሥጋዋ ትመክረው ጀመረች በብዙ ምሳሌ እያመሳሰለች ሥጋዬ ሞኝ ነህ መብልን አትውደድ ከአዳም ጀምሮ ከመጀመሪያው ሰው መብል ሲጎዳ እንጂ ሲጠቅም መቼ አየኸው /2/