አቤቱ ማረን ይቅር በለን /2/ ያለአንተ መድኃኒት የለን/2/ ሥጋዬን ብሉና ደሜን ጠጥታችሁ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኑራችሁ አቤቱ ----------------- ብሎ ነበር እርሱ የሚሰማው ጠፋ ሁሉም በየድርሻው ምኞቱን ሲያስፋፋ አቤቱ ------------- በሕይወት ለመኖር ትእዛዙን ጠብቀን ምኞት ሳነበዛ እናስብ ስሙን አቤቱ ------------ በሥጋው ቀድሶ ሲያድነን በደሙ ምን ውለታ ሠራን ለአምላክ በስሙ አቤቱ -------------------- ይህን ቅዱስ ሥጋ ይህን ክቡር ደም እንዴት ልጆች ብቻ በልተውት ይፈጸም አቤቱ ------------------ ብዙ ሰው ለግብዣ ተጠርቶ ነበረ ጊዜን በማሳለፍ ከዚያው ከደጅ ቀረ አቤቱ ----------------- ሌሎቹ በጥበብ ለመዳን ሲደክሙ ሕይወት የተገኘው በሥጋ ወደሙ አቤቱ --------