ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን /2/ የሰው ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጀመር ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር አንድ ቀን አይሞላም እንደአንተ አቆጣጠር /2/ አዝ . . . ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው ደካማ ነውና ሰው እድሜ ከራበው /2/ አዝ . . . እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ ምድርን በአበባ ሰማይን በኮከብ እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /2/ አዝ . . . ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ ደግሞም በጠቅላላ ዓለምን ብገዛ /2/ አዝ . . . በከንቱ ጊዜያችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ በርትተን ከሠራን ያለአንዳች ነቀፋ አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /2/ አዝ . . .