ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ከማቅረብ ከቶ አንወሰንም /2/ ዛሬም ወደፊትም ደግሞሞ ለዘለዓለም ስብሐት ለአብ -------- ከዚህ ከማራኪ ከኃላፊው ዓለም የጠራ ይድናል የፈጣሪውን ስም /2/ ሊኖረን ይገባል ፍቅርና ሰላም ስብሐት ለአብ --------------- ያልከውን አስበህ እናንተ ሁላችሁ ስሜን ከጠራችሁ ሁለት ሦስት ሁናችሁ እኔም እገኛለሁ በመካከላችሁ ስብሐት ለአብ --------- አቤቱ አምላክ ሆይ እንለምንሃለን እንድትገኝልን በመካከላችን /2/ ይኸው ተገኝተናል ሁለት ሦስት ሆነን ስብሐት ለአብ ------