በሞት ጥላ ወድቀን ስንከራተት/2/ በረቀቀው ፍቅሩ ዋጀን ከጥፋት /2/ በጎልጎታ የታይ ፍጹም መድኃኒት ሃሌ ሃሌ ሉያ ለአንድ ለኃያሉ ጌታ /2/ ስለእኛ ተዋረድክ በጎልጎታ የሞት ሸክም ከብዶን በጣር ስንባዝን /2/ ወረደ ከሰማይ መጣ ሊያድነን /2/ ከባርነት ቀንበር ነጻ ሊያወጣን አዝ --- ምንም ባልበደለ ምንም ባላጠፋው /2/ ሁሉን ማድረግ ሲቻል ደካማ የሆነው/2/ ሕይወትን ሊድለን ስለወደደን ነው አዝ --- እስቲ አስትውሉ የፍቅሩን ብዛት/2/ ለመስቀሉ ሞት ታዝዞ እኛን ያዳነበት/2/ ምንም አቻ የለው የጌታ ቸርነት አዝ ---