በዓለም ጥላ ማረፍ አይምስልህ ጤና ዓለም ከንቱ ጥላ ትሄዳለችና ዓለም ጥላ ስትሄድ ፀሐይ ስትበረታ ደግሞ ወድቆ ቀረ የሰው ልጅ አውታታ ተነሡ እንከተል እኛም ከሄዱት አፈር ከሸተተን ከያዘን በሽታ ብንቆርብ አንቀርም ይህን ጊዜ እንበርታ መቆረብ በሕይወት ነው ንስሓ መግባት ይህ ሁሉ አይገኝም ከገቡ መሬት ሰዎች ተጠንቀቁ እወቁ ሁላችሁ ዓለም አታላይ ናት እንዳታስቀራችሁ