ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ /2/ ሥጋውን እንብላ/3/ ደሙንም እንጠጣ የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው ተሰውቶልናል እንመገበው እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን እቀበል አምነን በልጅነታችን መቅረብ ወደጌታ (እግዚአብሔር) በእውነት የሚገባው በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው እንቅረብ ----------- ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት ከዋክብት ሰማይ የተነጠፋለት ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት እንቅረብ -------------- ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ ኑ እንቅረብ ---------------- ይህችን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት ከአሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ ኑ እንቅረብ ---------------