የሰው ልጆች ሁላችን እንማር አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር የሰው ልጆች ሁላችን እንማር መልካም ሥራን በመሥራት እንኑር የሰይጣን ድል መንሻ የክብር መውረሻ ሃይማኖት ናትና እውነተኛ ጋሻ አዝ --- ለእውነተኛ ሥራ ሁላችን እንበርታ ጻድቃን ሰማእታትን አድርገን መከታ አዝ --- ፍዳ ዓለምን አልፈን እንድንሄድ ሁላችን ጸንተን መገኘት ነው በሃይማኖታችን አዝ --- የሰይጣን ድል መንሻ የክብር መውረሻ ሃይማኖት ናትና እውነተኛ ጋሻ አዝ --- እምነታችን ሁሉ ይሁን በፈጠሪ ይቅር ባይ ነውና ሲቻለው መሀሪ