ላይቀር መሞት አፈር መልበስ መግባት ከመቃብር መስሎኝ ቋሚ ይህ ሥጋዬ ለእርሱ ብቻ ስጥር ግን ለነፍሴ ቀረ ማስታወሴ/2/ ዘመን መቁጠር እለት ወራት ክረምትና በጋ ሌትና ቀን ሲፈራረቅ ሲጨልም ሲነጋ በማየቴ ይሆን መደሰቴ/2/ ኸረ ወዲያ ወዲያልኝ ዋይ ይብላኝ ለነፍሴ አድርጎኛል የኃጢአት ምንጭ ደካማው መንፈሴ ላልኖር በዓለም ቆሜ ለዘለዓለም መሐሪ አምላክ ለጋስ ጌታ ቸሩ ፈጣሪዬ አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም ለእኔ መመኪያዬ ይቅር በለኝ ምሕረትህ አይራቀኝ/2/