ድንግል ሆይ ስለአንቺ ነውና መሐሪ አማልጅን ከአንድ ልጅሽ ከፈጣሪ ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አሣፈረኝ ድንግል ሆይ ---------------- ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ ትእዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ አዝ አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሣሪ አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ ድንግል ---------------- በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ ጻድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ አማልዱኝ ከአምላኬ ከአምላካችሁ ድንግል ሆይ ------------------