ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወዳንች መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም[፪] ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በእየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ[፪] ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በእየሩሳሌም ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት[፪] ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በእየሩሳሌም ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት[፪] ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በእየሩሳሌም የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው[፪] ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በእየሩሳሌም