ሆሣእና በአርያም ቅድስት ሀገር ሆይ ኢያሩሳሌም ምስጋናሽ ብዙ ነው በመላው ዓለም አዝ --- በአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው አዝ --- ኃይልና ሥልጣኑ በአንድ ላይ ስላለው ጠላቶች አፈሩ ሕዝብሽም ደስ አለው አዝ --- ሠውማ ቢዘምር ምን ያስደንቃል ሆሣእና ሰው ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል አዝ ---