ሆሣእና ብለን እናቅርብ ምስጋና ሆሣእና በሉ ሆሣእና ለወልደ አምላክ ሆሣእና ትኅትናን ላሳየን ›› ስሙ ይባረክ ›› አዝ --- ሆሣእና በሉ ›› ለሰማይ ንጉሥ ›› ግርማን ለብሶ መጣ ›› እኛን ሊቀድስ ›› አዝ --- ሆሣእና በሉ ሆሣእና ለወልደ ዳዊት ›› ነቢያት በትንቢት ›› የተናገሩለት ›› ሐዋርያት በወንጌል ›› የሰበኩለት ›› አዝ --- ሆሣእና በሉ ›› ለአምላከ ምሕረት ›› ተወልዶ ከድንግል ›› እንደ ሕጻናት ›› እረኞች በዋሻ ›› የሰገዱለት ›› የአዳም ልጆች ሁሉ ›› ደግሞም መላእክት ›› አዝ --- የትንሣኤ መዝሙር