አምላክ ተነሥቶአል የምስራች በሉ ሙስና መቃበር በኃይሉ አጥፍቶ ሁላችን አየነው ክርስቶስ ተነሥቶ አዳምን ለማዳን ቃል ኪዳን ገባለት ዘመኑን ጠብቆ ካሣ ሊከፍላት ከሰማያት ወርዶ የተሰቀለው ሞትን በሞት ሽሮ ይኸው አየነው ደቀመዛሙርቱ እጅጉን ተጨንቀው በጌታችን መሞት በሐዘን ተሞልተው በተዘጋ ደጃፍ ተሰብስበው ሳለ እጀቹን ዘርዓቶ ሰላም ለእናንተ አለ ማርያም መግደላዊት እየገሠገሠች በሌሊት ተነሥታ ወደ አምላኳ ሄደች አይሁድ አንገላተው የሰቀሉት ጌታን ተነሥቶ አግኝታ ተመላች በደስታ አዝ ---