እሰይ ተነሣ እሰይ እሰይ ተነሣ /2/ ተደመሠሠ በአምላክ የዓለም አበሣ ክብርና ምስጋና እሠይ እሠይ ተነሣ ይግባው ፈጣሪያችን እሠይ እሠይ ሞትን አሽንፎ እሠይ እሠይ አርዓያ የሆነን እሠይ እሠይ አዝ --- በከርሰ መቃብር ›› ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ›› ተቀብሮ አልቀረም ›› ተነስቷል በሰንበት ›› አዝ --- ለሐዋርያቱ ›› የምሥራች ያለች ›› ማርያም መግደላዊት ›› ምንኛ ታደለች ›› አዝ --- ዘበኞች ቢያቆሙ ›› አይሁድ ተሞኝተው ›› አልቻሉም ሊያስቀሩት ›› ሞትን ድል አደረገው ›› አዝ ---