የአምላክና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ ደስ ይበለን በትንሣኤው ብርሃን እልል እንበል በአንድነት ሆነን ተነሣልን መድሃኒታችን ከፊት ለፊት በመሣሉ የመስቀሉ ነገር የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ ሲያዝን ኖረ በምድራዊ ሕይወቱ ቢያሠቅቀው ሞቱ ግርፋሩ ሞኝነት ነው ለሚጠፋት መሠናከያቸው በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተስኗቸው ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው እውነተኛ የመዳን ቀን ዓርማ ነው ከገሃነም እሳት የሚያደን ነው እሰከመሞት ላስተለየው ቅዱስ ሐዋርያ ለዮሐንስ የወንጌል ሰው ለፅድቅ ባለሙያ ምስጋናችን በምድር ይድረሰው እንላለን በሰጠን ምሣሌው ሰዎች ሁሉ እንከተለው