በእኩለ ሌሊት ክርስቶስ ተነሣ /2/ ሙታን ይደለንም ክርስቶስ ተነሣ ሕያዋን ነን እኛ ክርስቶስ ተነሣ በመስቀሉ የዳንን ›› ከኃጢአት ቁራኛ ›› የተዋረደውን ›› ሊያከብር ዳግመኛ ›› ሞትን አሽንፎ ›› ተነሣልን ለእኛ ›› አዝ --- እናንተስ አትፍሩ ክርስቶስ ተነሣ እነግራችኋላው ›› የተሠቀለውን ›› እንድትሽ አውቃለው ›› ሕያዉን ከሙታን ›› ለምን ፈለጋችሁ ›› እንደተናገረው ›› ተነሥቷል ጌታችሁ ›› አዝ --- ክርስቶስ ሲነሣ ከርስቶስ ተነሣ በሰንበት ሌሊት ›› አስቀድሞ ታየ ›› ለመግደላዊት ›› እርሷም ትንሣኤውን ›› ለዓለም አበሠረች ›› ጌታዬን አየሁት ›› ተንስቶአል እያለች ›› አዝ ---