እልል /6 አማኑኤል ተነሣልን ደስ ይበልን ሁላችንን የሲኦል ደጆች ተከፈቱ እልል የሰይጣንም ሠራዊቶች አፈሩ እልል በጨለማው ዓለም ተወጠን ሳለን ጌታ በትንሣኤው ዛሬ አበራልን አዝ --- መቃብራት ሁሉ ተከፈቱ እልል የታሠሩ ነፍሳት ከግዞት ተፈቱ እልል መግደላዊት ማርያም ትንሣኤውን አይታ ነገረች ለሐዋርያት በደስታ ተሞልታ አዝ --- ሁለቱ መላእክት ብርሃን የለበሱ እልል ተነሥቷል አሏቸው ሴቶቹ ሲደርሱ እልል ሐዋርያት አይተው ዜና ትንሣኤውን አሏአቸው ለድኅነት ሰላም ለእናንተ ይሁን አዝ ---