ጠላት ድያብሎስን በሞቱ የረታ ከእኛ ጋራ ነውና የሠራዊት ጌታ ጨለማውን ኑሮ የሰደት ሕይወት በእግዚአብሔር ፍቅር ብርሃን በራበት ባርነት ቀርቶ ነጻነት ወጣን ልመናችንን እግዚአብሔር ሰማን አዝ --- መሠናክሉን ክፉውን ፈተና አልፈነው ወጣን በአምላክ ጎዳና አምላክ ከኛ ጋር ስለነበር ዲያብሎስ አፍሮ ተዋርዶ ቀረ አዝ --- የሚያስጨንቅ ዛሬ ተፈታ የሕዝቡን እንባ አበሰ ጌታ በምሕረቱ ስለጎበኘን አምላካችን ኑ እናመስግን አዝ ---