ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት /4/ በሕይወታችሁ ስበኩ በኑሮአችሁ ከጽንፍ እሰከ ጽንፍ በዓለም ዙሪያ አዳርሱ ሳትሰለቹ ደመና ጠቅሳችሁ እንደወፏ አዝ --- በኃጢአት ገመድ ተይዞ ለታሰረው በዓለም ጽልመት ለተዋጠው የእውነት መንገድ ብርሃን ለጠፋበት በሁለንተናው ፈንጥቁበት አዝ --- የጽድቅ እንጀራ በማጣት ለተራበው የሕይወታችን ውኃ ለተጠማው ቀቢፀ ተስፋ በልቡ ላደረባት የወንጌልን ማእድ አቅርቡለት አዝ --- አርድአተ ወንጌል ካህናት ሊቃውንት ለተልእኮ የጠራችሁ ከእውነተኛው ምንጭ ከጌታ ከባሕሩ ከሕይወትን ውኃ የጠጠችሁ አዝ --- ወይበሎሙ ሑሩ ወመሐሩ ለዘየአምን /2 ወንጌል መንግሥተ ሰማያት /4