መድኃኔዓለም /2 አረገ በክብር ደመና /2/ ተሰብስበው ሳሉ ሁሉም በአንድነት በመካከል ሆኖ ሥግው መለኮት ባረካቸው ቀደሳቸው አረገ በዓይን እየታያቸው /2 አዝ --- እንዲልክላቸው አጽናኙን መንፈስ ከላይ ከአርያም ከአባቱ ሲደርስ ኃይል ሆናቸው አጸናቸው /2 በቃሉ አንድ አደርጋቸው አዝ --- በአንድነት ሆነው ኢየሩሳሌም ተስፋ ሲጠብቁ ከላይ ከአርያም መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሣል /2 ወረደ በምሕረት ወሣህል አዝ --- መላእክት በሰማይ እልል እልል አሉ እርገቱን አጅበው ምስጉን ነህ እያሉ የሰማይ ደጅ ተከፈቱ ዘመሩ ሊቀመላእክቱ /2 አዝ ---