ከሊባኖስ ከሊባኖስ ከልጅሽ ጋር ነይ እመ አዶናይ ከሊባኖስ ወደእኛ ነይ ጥበቃሽ ዘወትር ከሊባኖስ እንዳይለየኝ ›› በሔድኩበት ሁሉ ›› ማረፊያ ሁኚኝ ›› አዝ --- እኔ ባሪያሽን ›› ድንግል አትርሺኝ ›› በጽድቅ ሠሌዳ ›› ስሜን ጻፊልኝ ›› አዝ --- ነፍስና ስጋዬ ›› አደራ እልሻለሁ ›› በልጅሽ ጽኑ ፍቅር ›› ተማጽኜሻለሁ ›› በልጅሽ ጽኑ ፍቅር ›› ተማጽኜሻለሁ ›› አዝ --- ከመሞት በፊት ለንስሓ አብቂኝ ለነፍሴ ማረፊያ አዘጋጂልኝ አዝ --- ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮች ተራራ መጥተሸ አስደስቺኝ እናቴ ሙሽራ አዝ --- የልብስሸ መዓዛ የሊባኖስ ሽታ ሮማን ናርዶስ ነው እናቱ ለጌታ አዝ --- እመቤቴ ስልሽ ስምሽን ስጠራ ፈጥነሽ ድረሺልኝ ከቅዱሳን ጋራ ፈጥነሽ ድረሺልኝ ከሚካኤል ጋራ ፈጥነሽ ድረሺልኝ ከገብርኤል ጋራ ፈጥነሽ ደረሺልኝ ከኡራኤል ጋራ