ኃጢአት በዓለም ነግሣ በድንግል መወለድ ቀረልን አበሣ እግዚአብሔር መረጠሸ ልትሆኚ እናቱ ይኸው ተፈጸመ የዳዊት ትንቢቱ አዝ --- የሔዋን ተስፋዋ የአዳም ሕይወት የኢያቄም የሐና ፍሬ በረከት ምክንያተ ድኅነት ኪዳነምሕረት ድንግል ተወለደች የአምላክ እናት አዝ --- በሔዋን ምክንያት ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘነው በድንግል ማርያም የምሥራች እንበል ሐዘናችን ይጥፋ ተወልዳለችና የዓለም ሁሉ ተስፋ አዝ ---