ሚካኤል ሚካኤል ገብርኤል ኡራኤል ሱርያል ወፋኑኤል/2/ ሚካኤል ሊቀ መላእክት አማልደን በምሕረትህ ልመናችን ቀርቧል ፊትህ/2/ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ሠለስቱ ዲቂቅን ከእሳት ያወጣህ በእውነት/2/ በሐዘናችን በመከራችን ቁምልን ከፊታችን ኡራኤል ነህ አለኝታችን/2/ ወላጆችን ሲጨንቃቸው እንዲፈታ ማኅፀናቸው ሩፋኤል ነህ ረዳታቸው