አማልደን ስንልህ ስማን እዘንልን/2/ አጽናን አረጋጋን/2/ ገብርኤል የእኛ መመኪያ አባታችን እግዚአብሔር ራሱ ክብርን አቀዳጅቶህ ለተልእኮ እንድትፈጥን አድርጎ የሾመህ እንደ ሦስቱ ሕፃናት አንተን እንደጠሩ ዛሬም አውጣን ገብርኤል ሆይ ከነፍሳችን ጠላት እምነት አለን እያልን የቀና ምግባር እባክህን ሊቀመላእክት እንድስት ርዳን መላእክትን ሁሉ ያረጋጋሀቸው እንተኮ ነህ ኃያል መልአክ ጽኑ ቁሙ ያልካቸው እኛስ እናምናለን በአማላጅነትህ በተሠጠህ በአምላክ ጸጋ ኃይላችን አንተ ነህ የምሥራች መልአክ ተብለሃልና ደስ አሰኘን ደስታ ስጠን ተጨንቀናልና ኢትዮጵያንም ታደግ ተዋሕዶንም ጠብቅ ሊቀመልአክት በል ቁምልን ሰይፍህንም ታጠቅ ሠራዊትህ ከበው እነርሱ ያጽናኑን ዘወትር ሳትርቀን ሰላምን ለግሠን አዝ----