ራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ ብርሃን ለባሽ እሳታዊው መልአክ አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ /2/ የራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ የምሥራች ነጋሪ ድንቅን ልደት አብሣሪ የጽድቅ ፋና የድህነት ጎዳና /2/ የራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ ላመኑብህ ለተማጸኑብህ ተጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ/2/ የራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው ከእሳት ነበልባል የ አዳንካቸው/2/ የራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ ምሰሶ ዐምዳችን መጠጊያችን ቅዱስ ገብርኤል ከለላችን/2/ የራማው ልዑል ገብርኤል /2/ ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ነዓ ስንልህ/2/ ዕለት ዕለት የምንማልድህ ልጆችህን ይምራን መንፈስህ /2/