ቅዱስ ገብርኤል ርዳን ሊቀ መላእክት /2/ ልጆችህን አውጣን ከሚነድ እሳት ልጆችህን አውጣን ከዓለም እሳት ከማይጠፋው እሳት ከዚያ ነበልባል ከጨለማው ሥርዓት ከክፉ ሲኦል ነፍሳችንን ነጥቆ ሰይጣን እንዳይጎዳን ዋስ ጠበቃ ሁነን ቅዱስ ገብርኤል ርዳን/2/ ረድኤት በረከትን ጸጋህ አይለየን እንለምንሃለን አደራ እንዳትርቀን የቀደመው ጠላት ዙሪያችን ከቦናል ቅዱስ ገብርኤል ድረስ የእግዚአብሔር ባለሟል/2/ ናቡከደነጾር ገደል ሲከታች እሳቱን አንድዶ ከእሳት ቢጥላቸው ከራሳቸው ፀጉር አንድ እንኳን ሳይጠፋ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ ሆነላቸው ተስፋ/2/ ብቸኝነት ከብዶን ሐዘን ሲያስጨንቀን እኛ እንጠራሃለን ቅዱስ ገብርኤል ብለን በፈጣሪያችን ፊት ስለእኛ ቆመሀል የነደደብንን እሳት አብርደሃል/2/ ሥልጣንህ ግሩም ነው በአምላክህ ፊት እንሠግድልሀለን የጸጋ ስግደት ፈጥነህ የምትሰማን ወዳንተ ስንጮህ .................................................... - 132 - የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ነህ/2/ አዝ ----