ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ /2/ ልብሱ ዘመብረቅ /፪/ ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ የወርቅ ልምላሜ /2/ ና /3/ ስለምንህ ቆሜ ገብርኤል ሊቀ መላእክት /2/ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት በሠለስቱ ደቂቅ ናቡከደነጾር ተቆጣ እሳቱ ነደደ ነበልባሉ ወጣ ግን ኃያል ገብርኤል ሊያድናቸው መጣ ገብርኤል ሊቀ መላእክት /2/ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት ሠለስቱ ደቂቅ ይባርክዎ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ብለው ምስጋና አቀረቡ ከእሳቱ ላይ ሆነው ገብርኤል ሊቀ መላእክት /2/ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት ራጉኤል ሊቀ መላእክት /2/ እመ ኀበ ላዕል ወረደ /፪/ መጋቤ ብርሃናት አንሶሳዌ ፋና ራጉኤል ና /5/ አማላጅ ነህና ራጉኤል ሊቀ መላእክት /፪/ እመ ኀበ ላዕል ወረደ /፪/ ዑራኤል ሊቀ መላእክት /2/ ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት በዓለም ፈተና በስቃይ ኩነኔ ስባዝን ስጨነቅ ስጠበብ ወይ እኔ ዑራኤል የእኔ ኃይል ቁምልኝ ከጎኔ ዑራኤል ሊቀ መላእክት /2/ ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት