ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡት ሥላሴ/2/ ተክለሃይማኖት ሆኗል ጠበቃ ለነፍሴ /2/ አዝ---------------- ዳሞት ይናገረው ያንተን ሐዋርያነት የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መላእከት /2/ አዝ ------------------ ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሃይናኖት ከሰው ልጅ ልቡና ይወጣል አጋንንት የቅዳሴው እጣን ሲወጣ ከዋሻው ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/ አዝ -------------- ከሱራፌል ተርታ ቆመህ በማጠንህ ሥሉስ ቅዱስ እያልህ ስታመሰግን ጸሎት ትሩፋትህ ትኅትና ስግደትህ ጾምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሠህ/2/ አዝ ----------------- ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው ሞቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው የጻድቁ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ ስድስት ክንፉ አወጣ ቢቆረጥ አንድ እግሩ /2/ አዝ --------- የኢትዮጵያን ምድር አረስከው በመስቀል ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል ትናንት የዘራኸው ዛሬም ለእኛ ሆንዋል አምላከ ተክለ አብ ብለን ተምረናል