ተነግሮ የማያልቅ ነው ጸጋህ /2/ በጸሎት የተጋህ የሃይማኖት ፍሬ ተክለ ሃይማኖት የወንጌል ገበሬ አዝ ----------------------- በወንጌል ብርሃን ሕዝቡን የመራኸው የኃጢአቱን ባሕር ከፍለህ ያሻገርከው ኢትዮጲያዊው ሙሴ በመስቀልህ ባርከን ፍሬ እንድናፈራ ንጹሕ አድርገን/2/ አዝ -------------------- ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት ወንጌል ያስተማርከው ለክርስቶስ መንግሥት ጠበልህ እንድምረን ውረድ አባታችን በእጣንህ መኣዛ ይፈወስ ደዌአችን /2/ አዝ -------------- ለማጠን የበቃህ የሥላሴን መንበር ሰይጣን ከቶም አይደርስ በሄድክበት ሀገር ለህሙማን ሁሉ የሆነካቸው ፈውስ ጠብቀን አቡዬ በሥጋም በነፍስ አዝ--------------- በጣሙን የበዛ ትሩፋት ምግባርህ ጸሎትህን ያልተውክ ቢቆረጥ አንድ እግርህ ምእራፈ ቅዱሳን የወንጌል ገበሬ እኛንም አድነን ከዘህ ኣለም አውሬ አዝ ---------------------