የአምላክን በረከት ጸጋውንም ሽተው በመከራ ጸኑ ከዲያብሎስ ታግለው በእምነታቸው ጽናት በእግዚአብሔር ጸጋ ቅዱሳን አባቶች አግኝታዋል ዋጋ የእምነቱ ገበሬ ተክለሃይማኖት በአምላክህ ታምነህ ድል አደረግኽ ጠላትን ፈጣሪ የሰጠኸን ረድኤት በረከት ለእኛም እንዲሠጠን ለምንልን ከአምላክ የአምላክ ባለሟል ገብረመንፈስቅዱስ ኢትዮጵያን አስማርካት በጾምና ጸሎት ታማኝ አገልጋይ ነህ ለኅብረተሰብህ ልጆችህን አስተምረን እንጓዝ በአንተ እግር ጻድቁ አባታችን ታማኝ አገልጋይ አቡነ አረገዊ ደስ ያሰኛል ሥራህ እንደ አምላክህ ፈቃድ በሕጉ ተመርተህ በዘንዶ ጀርባ ላይ ደብረ ዳሞ አየንህ ቅዱስ የሦስት ዓመት ሕፃኑ ቂርቆስ ገድልህ አስደናቂ የህሙማን ፈውስ እናትህ ኢየሉጣን በርቺ አይዞሽ እንዳልክ ልጆችህን ጠብቀን ከዲያብሎስ ተውሣክ አዝ -----------------