ተክለሃይማኖት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስቅዱስ አባታችን አማልደን አስታርቀን ከፈጣሪ ጋር ከአምላካችን/2/ በሦስት ቀን ሥላሴን ያመስገንህ ከጭንጫ ድንጋይ ውኃ ያፈለቅህ አባታችን ተክለሃይማኖት አማልደን በኃጢአት እንዳንሞት/2/ እንደ መላእከት ክንፍ የተሠጠህ ሰማእት ነቢይ አንድም ካህን ነህ መምህራችን ሐዲስ ሐዋርያ /2/ አስተምረን የጽድቅ ባለሞያ/2/ አዝ--------------- እንደ ሱራፌል በሰማይ ሲያጥን በምድር ላይ ረድእ ሆኖ ማገልገሉን በተሠጠው ጸጋ ሲያስነሣ ሙታን ክህነቱ ከአንተ ዘንድ ናት አባታችን ፍታን ከኃጢአት /2/ አዝ ------------------