ፊልጶስ አባታችን ፊልጶስ መምህራችን የተባረከ ነው ስምህ/2/ እኛ ልጆችህ/2/ ጠብቀን በጸሎትህ/2/ የኢትዮጵያ ባለውለታዋ ቅዱስ ፊልጶስ ነህ አድማቂዋ አዝ -------- ከእግዚአብሔር ተልከህ ወደ ጋዛ ምድረ በዳ ወረድህ ትንቢተ ወንጌልን የሠጠህ አንተ ነህ አዝ-------------- ቤተክርስቲያን ሠርታ በስምህ አንጻ ስለ መታሠቢያህ ፅላት አስቀርጻ እንድትጠብቃት ከሰይጣን ፍላጻ አዝ ----------------- በስምኦን ጥንቆላ ሕዝብ ያምን ነበር በወንጌል ስብከትህ ሕዝብ ወደ አምላክህ ዞረ አዝ ------ በከተማ ሁሉ ዞረህ ያስተማርክ ስለ አዳኝ ጌታ ብለህ የሠበክ ድውያንን ፈወስህ ጸጋ ተሠጥቶህ አዝ ------------------