አምላክ በከበራት በተክለሃይማኖት ደጅ/2/ በረከት ይገኛል ከጻድቁ እጅ/2/ በመከራ ጊዜ ተክለ ሃይማኖት በችግሯ ቀን ተክለ ሃይማኖት እንደ ደረስክላት ተክለ ሃይማኖት እግዚእ ኀረያንን ተክለ ሃይማኖት እኛን ታድነን ዘንድ ተክለ ሃይማኖት አንተ ደግ አባት ተክለ ሃይማኖት መጥተናል ከቤትህ ተክለ ሃይማኖት ከያለንበት ተክለ ሃይማኖት አዝ------------- ከአምላክ በተሠጠህ ተክለሃይማኖት በቃል ኪዳንህ ተክለ ሃይማኖት ህሙማን የሚያድን ተክለ ሃይማኖት የንፈሮ ውኃህ ተክለ ሃይማኖት ድውይ የሚፈውስ ተክለ ሃይማኖት ግሩም ጸበልህ ተክለ ሃይማኖት ዘለዓለም ይኖራል ተክለ ሃይማኖት በዓለም ሲያሰጠራህ ተክለ ሃይማኖት አዝ ----------- ለ29 አመት ተክለ ሃይማኖት ተክሎ ጦሮችን ተክለ ሃይማኖት ለእኛ ለልጆቹ ተክለ ሃይማኖት ተስፋ ለቆረጥን ተክለ ሃይማኖት ደከመኝ አላለም ተክለ ሃይማኖት ቆሞ ሲጸልይ ተክለ ሃይማኖት አዝ ---------- የቅዱሳን ሀገር ደብረ ሊባኖስ ደብረ ሊባኖስ ደብረ ሊባኖስ ታጥራ ትኖራለች ደብረ ሊባኖስ በመንፈስቅዱስ ደብረ ሊባኖስ በቅዱሳን ጸሎት ደብረ ሊባኖስ ስለተቀደሠች ደብረ ሊባኖስ ለአድባራት ሁሉ ደብረ ሊባኖስ በክብር ትበልጣለች ደብረ ሊባኖስ አዝ --------------