ልቡና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ ኅሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው ቤ/ክ ናት አምባ መጠጊያቸው የመላእከት ዜማ የአእዋፍ ዝማሬ የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ አዝ ------------- ይዘምሩበታል በአንድነት ተባብረው የሌዋዊው በትር ጸናጽል ከበሮው አዝ ------------- ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ የእምነት አርበኞች ያገኝዋት በፍልሚያ አዝ ----------------- መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው አዝ ---------------------- ከኃጥአን ድንኳን መውጣቴ ነው ዛሬ የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ