ተክለሃይማኖት ፀሐይ የኢትዮጵያ ሲሣይ ምእራፈ ቅዱሳን /2/ በነፍስም በስጋ አትለየኝ የቅዱሳን አርእስት የዋሻው ብርሃን የጸሎት ባለቤት የነዳያን መድኅን ገና ስትወለድ አምላክ የመረጠህ የድውያን እምነት ፈዋሹ አንተነህ/2/ አዝ ------------------ ገና በሦስት ቀን በሕፃንነትህ ጌታን አወደሰው ቅዱስ አንደበትህ ደግሞም እግዚአብሔር አስቦሃልና በወጣትነትህ ወጣህ ለምነና/2/ አዝ------------ ሌትና ቀን ሳትመርጥ ክረምትና በጋ ስትጸልይ ውለህ ስትጸልይ ነጋ በመቆምህ ብዛት አንድ እግርህ ሲነሣ ጸሎትህን ፈጸምክ ለሥጋ ሳትሣሣ/2/ አዝ---------- ምንኛ ድንቅ ነው ቅዱስ የአንተ ብርታት 7 ዓመት ሙሉ በአንድ እግርህ ጸሎት የዓለም ግሣንግሷ ሀብቷ ሣይስብህ ለኢትዮጵያ ጸለይክ ቆመህ በአንድ እግርህ/2/ › አዝ --------- የሃይማኖት ተክል የኢትዮጵያ አባት ምሕረት ከአምላክ ለሀገርህ አሠጣት እኛንም አግዘን ጽድቅን እንድንሠራ በተሠጠህ ሥልጣን ጠብቀን አደራ/2/ አዝ --------------